Description
ይህ ትዝታ፣ ፖለቲካ እና ሠማያዊ በሚል ርእስ ያሰናዳሁት መጽሃፍ አሰብ፣ አይሳኢታ፣ ሠመራ፣ ጎንደር እና አዲስ አበባን ያካልላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ “ፖለቲካ” የሚባለውን ቃል ከሰማሁበት የልጅነት አእምሮዬ በመጀመር እኔም ለአቅመ ፖለቲካ ደርሼ በመሳተፍ ያለፍኩበትን፣ ያስተዋልኩትንና በማስታዎሻዬ ተሰድረው የነበሩ የወቅቱን የእውነት ሂደት ያሳያል፡፡ ሠማያዊ ፓርቲ ውስጥ ስናከናውናቸው የነበሩ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ስብሰባዎች ስልታዊ (ስትራቴጅክ) ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ ዋናው ዓላማ ስልታዊ መሆን አለመሆናቸው ሳይሆን ትዝታን፣ ፖለቲካን እና ሠማያዊን በማሰናሰን የአንድ ወቅት ታሪክ የነበረ ስለሆነ ለተዋናዮቹ፣ ለታዛቢዎቹ ለመጭው ታሪክ ተረካቢ ማሳየትንና አቆይቶ ማውረስን መሰረት ያደረገ ሲሆን ተተኪው ትውልድ የራሱን መረዳት እንዲያገኝ እድል መስጠት ላይ ያተኮረ ነው፡፡









Reviews
There are no reviews yet.