Description
ሰው በተፈጥሯዊ ኑባሬው ደስተኛ፣ ጤናማ፣ በሀሴት የተሞላ፣ ኑሮው የተቃና እንዲሆን ይሻል፡፡ ሰዎች በማለዳ ከእንቅልፋቸው ሲነቁና ቀኑን ሲጀምሩ በጉጉት ሊሆን ይገባል፡፡ ከሰዎች ጋር በሚኖር ግንኙኘትና መስተጋብር ሁልጊዜ ደስተኛ እና በመልካምነት የተቃኘ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በየቀኑ የሚተገበሩ የትኛውም እንቅስቃሴዎች ወደላይ አልያም ወደፊትና ግብን ማሳካት በሚቻልበት አቅጣጫ መሆን እንዳለበት መዘንጋት የለበትም፡፡ በሀገርኛ ብሒልም “ወደፊት መውደቅ” የሚባለው ለዚህ ገላጭ አባባል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በየትኛውም ጊዜ እና የህይወት ውጣ ውረድ ምስጋና ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ በኑሯችን አጋጣሚ ሁሉ ከላይ ከተጠቀሰው የህይወት መርህ ሳይተገበር ከቀረ እንዲሁም እንደታሰበው ካልሆነ ያልተስተካከለ የኑሮ ቀመር አለ ማለት ነው፡፡ በህይወት እንደ ቀዳሚ መርህ መወሰድ ያለበት ኑሮን ደስተኛ፣ ቀና እና ስኬታማ ለማድረግ እንዲሁም ተስፋ አስቆራጭና አሉታዊ እሳቤን በማስወገድ አወንታዊ አእምራዊ ሁናቴ መፍጠር ነው፡፡









Galiliyo Galili (verified owner) –
መጽሐፉ በጣም በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ነው። ወድጄዋለሁ!!