Description
ብሩክ ካብታሙ
ከአለማያ ዩኒቨርስቲ (ኢትዮጵያ) የመጀመሪያ ዲግሪውን በግብርና ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ ከአበርዲን (ስኮትላንድ – እንግሊዝ) ዩኒቨርስቲ በግብርና ኢኮኖሚክስ ተመርቆ፣ በኢትዮጵያ፣ በሱዳን፣ አፍጋኒስታንና ዚምባብዌ ተዘዋውሮ ለብዙ አመታት በተለያዩ የቴክኒክና የሃላፊነት ቦታዎች ሰርቷል። አሁን ደግሞ በሲቪል ማህበራት ባለሞያነት ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰራ ይገኛል።
አጫጭር ግጥሞችንና ቴያትር በመድረስ ለአለማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በማቅረብ የጀመረውን ስነጽሁፍ አሳድጎ፣ እነሆ አሁን ደግሞ አጫጭር እውነተኛና ልብወለድ ታሪኮችን የያዘ መጽሐፍ ይዞልን መጥቷል። “ምርቃት”፣ “የጨርቆስ ልጅ”፣ “ካምፖሎጆ”፣ “የኛ ግቢ – የኛ አገር” እና “ከዳቦ ቅርጫትነት ወደ መለመኛ ኮሮጆነት” የተሰኙትን ታሪኮች ከእውነተኛ የህይወት ገጠመኞቹ ጨልፎ በጥሩ አቀራረብ ሲተርክልን፣ ሰባት አጫጭር ልብ ወለድ ታሪኮችን አካቶ እነሆ ለአንባቢያን አቅርቧል።










Reviews
There are no reviews yet.