Sale!

ቃልና ተግባር ሲለያይ

Original price was: Br 450.00.Current price is: Br 200.00.

Book Information


መደብር
0 out of 5

ባለፉት ሀምሳ ዓመታት መንግሥታትና የፖለቲካ ኃይሎች ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ የገቧቸው ቃሎች ተፈፅመዋል? ካልተፈፀሙስ ባለመፈፀማቸው ምን ተፈጠረ? መልሱን ከመጽሐፉ ያገኙታል።

  ጥያቄዎ ወይም አስተያየትዎ
SKU: BMC-MB6939 Categories: , , ,

Description

ቃልና ተግባር ሲለያይ ስለመጽሐፉ አጭር መግለጫ

መጽሐፉ በዘጠኝ ምዕራፎች የተከፈለ በውስጡ ከ60 በሊይ አጫጭር ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተና በ365 ገጾች የተዘጋጀ ነው፡፡ መጽሔፉ በኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት የተለዋወጡ መንግሥታትና መሪዎቻቸው፤ ሌዩ ሌዩ የመንግሥት ተቋማትና የጦር መሪዎች፤ ገዥና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፓርቲ መሪዎችና ተከታዮቻቸው፤ የሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት፤ የሀይማኖት ተቋማት፣ መሪዎችና ተከታዮቻቸው ሀገርና ሕዝብን እንዴት እንደሚበድሉ፤ ለሀገርና ለሕዝብ የሚገቡትን ቃሌ እንዴት እንደሚያጥፉ፤ የገቡትን ቃል ዘንግተው ያልተገቡ ተግባራትን  እንደሚፈፅሙና ሀገርና ሕዝብን እንዴት እንደሚዋሹ፣

ፀረ- ኢትዮጵያ የሆኑ የውጪ መንግሥታትና ፖለቲከኞች፤ የእነሱ ተላላኪ፣ ተልዕኮ ፈፃሚና አስፈፃሚ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በፖለቲካና በትጥቅ ትግል ሥም በውጪና በጎሬቤት አገሮች ውስጥ የሚመሽጉ የፖለቲካ ቡድኖች፤ እንደዚሁም ፅንፈኛና ሀይማኖት ለበስ ፖለቲከኞች፤ የውጪና የሀገር ውስጥ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች እና የእነዚህ ተከታይና አጃቢ የሆነው ዳያስፖራ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እንዯዴት እንደከፋፈሉ፤ የሀገርና የሕዝብን መብት፣ ክብርና ነፃነትን እንዴት ለባዕዳን አሳልፈው ሲሰጡ እንደቆዩ በዝርዝር ያስረዳሌል፡

መጽሐፉ ከአፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥት ጀምሮ ያሉ መንግሥታት ለሀገርና ለሕዝብ ምን ቃሌ ገቡ፤ ቃላቸውን መተግበር ለምን አቃታቸው? በነዚህ መንግሥታት ዘመን በግልጽና በህቡዕ፣ በሠላማዊና በኃይል (በትጥቅ) ትግል ተደራጅተው የታገሉ ቡድኖችና ፓርቲዎች ሀገርና ሕዝብን ጠቀሙ ወይስ ጎዱ ዓላማና ግባቸውን ስሌጣን መያዝና ለስሌጣን ብቻ አድርገው የተነሱ የፖለቲካ ቡድኖችና አመራሮቻቸው ኢትዮጵያን ታደጓት ወይስ ወደ ማጥ ውስጥ ከተቷት የሚለውን ከነማሳያዎቹ እያቀረበ ይሞግታል፡፡

መጽሐፉ የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት በብሔራዊ የግዛት አንድነትና የግዛት ወሰን፤ በብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ፤ በብሔራዊ ቋንቋና በብሔራዊ መዝሙር ላይ የፈጠረውን ችግርና በሕገ- መንግሥቱ ላይ የተሠራውን ጥልቅ ሴራ ያብራራሌ፡፡ በእያንዳንደ ምዕራፍ በሚያነሳቸው ጉዳዮች ሊይ …ቢሆን ኖሮ…የሚላቸውን እና ለወደፊትም መፍትሔ ሊሆን ይችላል የሚላቸውን ጉዳዮችንና ሀሳቦችን ያነሳል፣ ይተነትናል፣ በዝርዝር ያብራራል፡፡ በአጠቃላይ ደራሲው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከ30 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ የታዘባቸውን እውነታዎችን በዝርዝር ያሳያል፡፡

Reviews

There are no reviews yet.

Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.

General Inquiries

There are no inquiries yet.

Buy

0
YOUR CART
  • No products in the cart.