Description
የማስታወቂያ ሥራ ገቢ ከሚያስገኙ የሥራ ዘርፎች አንዱ ለመሆን በቅቷል ፡፡ ይኸው ዘርፍ በሙያነቱና በገቢ ማስገኛነቱ ታምኖበት ሥራዬ ተብሎ ከተያዘም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ጥያቄ የሆነባቸው አንዳንዶች ዛሬም ድረስ የማስታወቂያ ሥራ ሙያ የመሆኑን ነገር ይጠራጠራሉ፡፡ ነገር ግን ማስታወቂያ አውቀነውም ሆነ ባለማወቅ ከዕለት ተዕለት ኑሯችን ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው፡፡ የማስታወቂያ ሥራ ሙያነትን ያመኑት አንድ ምርት ወይም አገልግሎት የተፈለገውን ያህል ገበያ ያገኝ ዘንድ ማስታወቂያ ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉ ይናገራሉ፡፡ ገበያተኛው ምርጫውን ያሰተካክል ዘንድ ማስታወቂያ መረጃም ነው ሲሉ ብዙዎች ጽፈዋል፡፡
ይህ የማስታወቂያ መሠረታዊ መርሖዎች፤ ቅጽ ፩ መጽሐፍ ስለማስታወቂያ ሙያ መሠረታዊ ዕውቀቶችን ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ በዚህም ስለሙያው ምንነት የሚያብራሩ መሠረተ – ሐሳቦች፣ ስለታሪካዊ አጀማመሩ መጠነኛ ፍንጭ የሚሰጡ፣ ማስታወቂያን የማዘጋጀት ብልኀቶች፣ የማስታወቂያን ውጤት ስለመለካትና ስለሙያው ሥነ – ምግባር መርሖዎችና ደንቦች የሚመለከቱ ጉዳዮችን በዝርዝር ያነሳል፡፡









Reviews
There are no reviews yet.