Description
በሀገራችን ኢትዮጵያ የወጣቶችን ሕይወት በተመለከተ የተጻፉ መጽሐፍት እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም። እነዚህ መጽሐፍት አብዛኞቹ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው ሆነው ትኩረታቸውም ስለ ትዳር እና ጋብቻ፣ የልጆች አስተዳደግን በተመለከተ የተጻፉ ናቸው። በትምህርት ተቋማት እና በግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሚጻፉት መጽሐፍት እና የሚታተሙት የምርምር ጽሑፎች ደግሞ አብዛኞቹ የሥነ-ተዋልዶ ሕይወትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው። አሁን አሁን ደግሞ ወጣቱን ልቅ ወደ ሆነ ወሲብ የሚገፋፉ ዝሙትና አመንዝራነት የተጠናወታቸው መጽሐፍት እየተጻፉ እየወጡ ነው። ስለ ትዳር፣ ፍቺ፣ ወሲብ፣ ፍቅር፣ የልጆች አስተዳደግ ብዙ ጊዜ ይነገራል። ስለ ትዳር ሲነገር ወይም ሲጻፍ የትዳር ቅድመ ሁኔታዎችን የሚባሉትን ፍቅር፣ የገንዘብ አቅም፣ አካላዊ እና አእምሯ ብቁነት፣ ወዘተ. ይነገራል። በትዳር ውስጥ ጸንቶ ለመኖር ፍቅር፣ መቻቻል፣ መተማመን፣ መከባበር ብዙ ጊዜ ተነግሯል። ስለ ወሲብ ሲነገር ደግሞ ወሲብ ስለሚያስገኘው እርካታ፣ በወሲብ አለመጣጣም••••••••










Reviews
There are no reviews yet.