Description
ፀሐፊው አቶ ወልደሔር በመጽሐፉ መግቢያ ላይ “ወልደሔር ይዘንጋው እባላለሁ፡፡ ሔር ማለት ቸር ማለት ነው፡፡ ቸር ደግሞ በወንጌል እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር ነው፡፡ ስለሆነም ወልደሔር ማለት ወልደ እግዚአብሔር፣ ወይም የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ነው፡፡
….እናም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ’ዚች ምድር መጣሁ፡፡ በዚች ምድር ከልፋት ኑሮና ከመቃተት ሕይወት ያካበትሁትን እውቀትና ልምድ፣ ወደ ስኬት ያደረሰኝንም መንገድ ለወገኖቼ ላ’ሳውቅ ወደድሁ፡፡
ወገኖቼ…! የሰው ልጅ ተወልዶ ማለፉ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ሞትን ያመጣው የመጀመሪያው የሰው ልጅ ልደት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ሞትም ሆነ ልደት ሁለቱም የፈጣሪ ምስጢራት ናቸው፡፡ ሰው የሚወለድበትንም ሆነ የሚሞትበትን ቀን አያቅም፡፡ ራቁቱን ተወልዶ ኖሮ-ኖሮ እራቁቱን ወደ እዚያኛው ዓለም ይሸኛል፡፡
በዚህ የተፈጥሮ ሕግ መሠረት ተወልደን፣ አድገን፣ ወደ እማይቀረው ሞት እስከምንሄድ በሰላምና በጸጋ መኖር የምንችለው፣ ለአገራችን ዕድገት፣ ለሕዝባችን ደህንነት፣ ለራሳችን ብልጽግና ሌት-ተቀን ተግተን ስንሠራ ብቻ ነው፡፡” ብለዋል።









Reviews
There are no reviews yet.