Additional information
| Authors | ካሣ አያሌው ካሣ |
|---|---|
| Publication Year | 2009 ዓ.ም |
| Title | አቫንቲ ወደጥቁሩ ገዳም |
| ISBN | 1234567890123 |
Br 100.00
በአንደበት ሊገለፅ የማይቻል የሰው ልጆች ታላቅ ምስጢር እዚያ ተሰውሮ ዓለምን እየተጠባበቀ ነው………………….
የእረስ በእርስ ጦርነት ኢትዮጵያን እያመሳት ነው፡፡ አንድ ካህን ደግሞ በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ታስረው ሞታቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ካህኑ ላለፉት አራት አስርት አመታት የውጭውን ፀሀይ ለማየት አልታደሉም፡፡በዚያች ወሳኝ ሰዓት የከባድ መሳሪያ ፍንዳታ የታሰሩበትን አካባቢ አናውጦ ከፍተኛ ጉዳት አስከተለና፤ ታሳሪውንና አብሯቸው የተቆለፈበት ሚስጥራቸውን ነፃ ለማውጣት በቃ፡፡
በዚህች ወሳኝ ሰዓት……… ሁለት ጋዜጠኞችና አንዲት ውብ የፎቶ ግራፍ ባለሙያ እኝህን በጦር መሳሪያ ተኩስ የቆሰሉና የደመ ነፍስ ጉዞ ላይ የነበሩ ሰው በጥቅጥቁ ደን ውስጥ አገኟቸው፡፡አግኝተዋቸውም ነፍሳቸውን ለማትረፍ ሲረባረቡላቸው እርሳቸውን ለዘመን አቋራጭ የእስር ቤት ህይወት ያበቃቸውን ፍፁም ሊታመን የማይችል አስደናቂ ታሪክ አወጓቸው፡፡ስለ ቅዱሱ ፅዋ ትክክለኛ የመገኛ ስፍራ …………
በዚህ ምክንያትም ጋዜጠኞቹ በፍፁም ሊሞከር ቀርቶ ሊታሰብ ለማይችል አሰሳ መንገድ አልባ ጉዞ ውስጥ ገቡ፡፡ይህ እንቅስቃሴያቸውም በጨካኝ ሽፍታዎችና ምህረት በሌላቸው የግድያ ውሳኔዎች መካከል ሲያንገላታቸው እንዲሁም በአስገራሚ የገዳም መነኮሳት እጅ ሲጥላቸው ከረመ፡፡በመጨረሻም ከማንነታቸው የሚገናኙበትና ምንነታቸውን የሚረዱበት የሚስጥሩን ቁልፍ አቀዳጃቸው፡፡
‹THE QUEST› በጥንታዊውና ነባራወዊው አፈ ታሪክ፤እንዲሁም አደገኛ የዱር መካከል ጦርነቶች ላይ ፋና ወጊ ጥናት አካሂዶ የተፃፈ፤ ማንንም አንባቢ ንባብ ካስጀመረ ሳያስፈፅም የማይለቅ ጥልቅ የስነ ፅሑፍ ውጤት ነው፡፡በስውርና የተቀበሩ ሚስጥራቷ፤ እንዲሁም በተሸሸገ ማንነቷ የሁሉን ተመራማሪ ቀልብና ስሜት ከምትገዛ አገረ ኢትዮጵያ የተቀዳ መሳጭ ታሪክ……………………
| Authors | ካሣ አያሌው ካሣ |
|---|---|
| Publication Year | 2009 ዓ.ም |
| Title | አቫንቲ ወደጥቁሩ ገዳም |
| ISBN | 1234567890123 |
Only logged in customers who have purchased this product may leave a review.
There are no inquiries yet.




Reviews
There are no reviews yet.